የሀገር ውስጥ ዜና

የለውጡ ትሩፋት የሆኑ ሴት አመራሮች መድረክ እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

August 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የለውጡ ትሩፋት የሆኑ ሴት አመራሮች መድረክ በሳይንስ ሙዚዬም እየተካሄደ ነው፡፡

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጀው መርሐ ግብሩ “የኢትዮጵያ ሴቶች ከየት ወዴት” በሚል ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የሴቶችን ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ተሳታፊነት በማጎልበት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እምቅ አቅምን ወደ ተገባር ለመቀየር የሚያስችል ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!