የሀገር ውስጥ ዜና

በሐሳብ ላይ የመነጋገር ባህል እንዲዳብር ፖለቲከኞች ልምዳቸውን ሰንደው ሊያስቀምጡ ይገባል – ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

August 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐሳብ ላይ የመነጋገር ባህል እንዲዳብር ፖለቲከኞች ልምዳቸውን ሰንደው እና በመጻሕፍት አዘጋጅተው ለሚቀጥለው ትውልድ ሊያስቀምጡ ይገባል አሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)።

“ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ” በሚል ርዕስ መጽሐፍ የጻፉት ተስፋዬ (ዶ/ር)÷ መጽሐፉ ከወጣ በኋላ እኔ ካለሁበት የፖለቲካ ፓርቲ ውጭ ከተፎካካሪ ፓርቲ እና ከገለልተኛ ሰዎች በተሰጡኝ አስተያየቶች ኢትዮጵያዊያን ሐሳብ ላይ ለመነጋገር ክፍት መሆናቸውን ተረድቼበታለሁ ብለዋል።

ሚኒስትሩ ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ሐሳቦች ተሰንደው ከቀረቡ ኢትዮጵያዊያን ካለፈው ታሪክ በመማር ከመጠፋፋት ይልቅ ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን እንደተረዱ አንስተዋል።

ዴሞክራሲ የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ዓለም አቀፋዊ ቢሆንም ሀገራት ባላቸው እሴት ላይ ተመርኩዘው ከሕዝቡ ባህል ጋር አብሮ የሚሄድ ዴሞክራሲን ሲገነቡ ሀገራዊ ማድረግ ይቻላልም ነው ያሉት።

ዴሞክራሲ ማለት እንከንአልባ የአስተዳደር ሥርዓት ማለት አለመሆኑን ጠቅሰው÷ ከሌሎቹ የአስተዳደር ሥርዓቶች የተሻለ እና የተመረጠ እንደሆነ የሚታመንበት መሆኑን አመላክተዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስት ጋር የነበራቸውን ቆይታ ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ👇👇https://www.youtube.com/watch?v=ozu7aXjsnbo

በብርሃኑ አበራ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!