አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ስኬታማነት ሰላምን ማጽናት የሁሉም ኃላፊነት መሆን አለበት አሉ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ።
በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የሰላምና ጸጥታ ዘርፍ አመራሮች በአዳማ ያካሄዱት የምክክር መድረክ ተጠናቋል።
በማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስትሩ ሰላምን እና ልማትን በማቀናጀት መተግበር ይገባል ብለዋል።
ለሀገር ግንባታ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ጠቁመው÷ የሀገርን ከፍታ ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፎች ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
የሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑን ገልጸው÷ ባህላዊ የችግር አፈታት ስርዓቶችን ለሀገር ግንባታ የመጠቀም ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ለመጪው ትውልድ ሁለንተናዊ ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ሀገር ለማስረከብ እየተሰራ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!