የሀገር ውስጥ ዜና

በሀረር ከተማ በታቀደላቸው ጊዜና ጥራት እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች…

By Adimasu Aragawu

August 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረር ከተማ የቱሪዝም ዘርፉን የሚያሳድጉና የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ናቸው አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።

አቶ ኦርዲን በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የአባድር ፕላዛ፣ የሀረር ላንድ ማርክ የኮሪደር ልማት፣ የመሶብ አንድ ማዕከል፣ የሀማሬሳና ኢኮፓርክ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝታቸውም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

በተለይም በሀረር ከተማ እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የከተማውን እድገት የሚያፋጥኑ፣ የቱሪዝም ዘርፉን የሚያሳድጉና የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።

ፕሮጅቶቹ ተቋማዊ የመፈፀም አቅም፣ ቅንጅትና ቁርጠኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ መምጣቱ በተግባር የታየበት መሆኑን አቶ ኦርዲን አንስተዋል።

ህዝብን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የሀረርን የማንሰራራት ዘመን እውን ለማድረግ ከማስቻል ባሻገር ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ጉልህ ሚና እያበረከቱ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

በቀጣይም ጥራትና ፍጥነትን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ስራ ይሰራል ብለዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!