የሀገር ውስጥ ዜና

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በልዩ ድምቀት ይከበራል – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

By Adimasu Aragawu

August 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በልዩ ድምቀት ይከበራል አሉ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር።

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀንን በተመለከተ አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት የዐቢይ ኮሚቴ አባላት የመጀመሪያውን የመሪ ዕቅድ ውይይት እያካሄደ ነው።

አፈ ጉባኤ አገኘሁ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ 20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚከበር መሆኑ የለውጡ መንግስት ጥያቄን የመመለስ ተግባራዊ ትሩፋትን የሚያሳይ ነው።

ቀኑ በልዩ ድምቀት እንደሚከበር አንስተው÷ ለዓመታት በልሂቃን መካከል ሲስተናገድ የነበረው ከፍተኛ የልዩነት ችግር ለመፍታት እንደ ሀገር ምክክር የሚደረግበት መሆኑን ጠቁመዋል።

በመድረኩ የሁሉም ክልል አፈጉባኤዎች፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዴኤታዎች ተገኝተዋል፡፡

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ኅዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል።

በይስማው አደራው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!