የሀገር ውስጥ ዜና

ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ የዕጅ መንሻ በማቅረብ የተጠረጠረው ቻይናዊ ተከሰሰ

By Abiy Getahun

August 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ‘ጉዳዬ በአፋጣኝ እንዲፈፀምልኝ’ በማለት የዕጅ መንሻ በማቅረብ የተጠረጠረ ቻይናዊ ክስ ተመሠረተበት፡፡

ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ የሙስና ወንጀሎች ችሎት ነው።

ተከሳሹ ሊ ሆንግ ኩዌ የተባለ ቻይናዊ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 25 (5) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ነው ክሱ የተመሠረተበት፡፡

የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ተከሳሹ ዳ ቻንግ ኤሌክትሪክ ፓወር ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለ ድርጅት ባለቤት ሆኖ ሲሰራ በሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ድርጅቱ አዲስ የትራንስፎርመር አምራች መሆኑን በመጥቀስ የአምራችነት ማረጋገጫ ፍቃድ እንዲሰጠው ላቀረበው ጥያቄ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው ለተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ለሆኑት 1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በዕለቱ በነበረው የምንዛሪ ተመን 133 ሺህ 356.6 ብር ስጦታ ያቀረበ በመሆኑ በፈጸመው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡

ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱ የተነበበለት ሲሆን ለጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓም ቀጠሮ ተሰጥቶታል።

በመቅደስ የኔሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!