ቴክ

ከ308 ቢሊየን ብር በላይ ግዥ በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት…

By Melaku Gedif

August 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ከ308 ቢሊየን ብር በላይ ግዥ በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ተፈጽሟል አለ የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ እንዳሉት ÷ በበጀት ዓመቱ የመንግሥት ግዥና አስተዳደር ሥርዓትን ዘመናዊ ከማድረግ አንፃር አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በ169 የፌዴራል ባለበጀት ተቋማትና 93 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም 308 ነጥብ 75 ቢሊየን ብር በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት መፈጸሙን ነው የተናገሩት፡፡

300 ቢሊየን ብሩ በጨረታ እንዲሁም 8 ነጥብ 75 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ዋጋ በማቅረብ የግዥ ሒደት መከናወኑንም አብራርተዋል።

በ2016 በጀት ዓመት በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት የተከናወነው የመንግስት ግዥ 65 በመቶ ሲሆን÷ በ2017 በጀት ዓመት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት መፈጸሙን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!