አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ኢኒሼቲቭ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ነጥረው እንዲወጡ እና ስታርታፕ ቢዝነሶች እንዲስፋፉ እያደረገ ነው አለ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፡፡
ኢኒሼቲቩ ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሥነምህዳር እንዲመሰረት ማስቻሉም ተገልጿል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አማካሪ አብዮት ባዩ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በኢኖቬሽን እና አርቲፊሻል አንተለጀንስ በርካታ ወጣቶችን የግዙፍ ኩባንያዎች ባለቤት ለማድረግ እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት ሰፊ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች መሰራታቸውን ጠቅሰው÷ ዘንድሮ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎች የራሳቸውን ቢዝነስ እንዲመሰርቱ እድል እየተመቻቸ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ሁለተኛው ዙር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ኢኒሼቲቭ ይቀጥላል ያሉት አብዮት (ዶ/ር)÷ ዲጂታላይዜሽን ለስራ እድል ፈጠራ እና የፈጠራ አቅምን ለማጎልበት አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
በጸጋዬ ንጉስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!