አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እሸቱ ወንጨቆ (ፕ/ር) የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል፡፡
የስታትስቲክስ ምሁሩ እሸቱ ወንጨቆ (ፕ/ር) በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን፣ በፈረንጆቹ ከ2001 እስከ 2002 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በተቋሙ ሰራተኞች የተመረጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል።
እሸቱ (ፕ/ር) ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የሥራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል።
በዐምደወርቅ ሽባባው