የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ 25 ቢሊየን ብር የሚገመት አገልግሎት ይሰጣል

By Melaku Gedif

August 13, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በዘንድሮ ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 25 ቢሊየን ብር የሚገመት አገልግሎት ይሰጣል አለ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ከድር እንዳልካቸው ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

በ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 10 ሚሊየን ያህል ወጣቶችን በማሳተፍ የተለያዩ 34 ዓይነት ስራዎች እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በከተማ ውበት እና መሰረተ ልማት፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በጤና መስኮች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተለይም በአረንጓዴ አሻራ፣ በደም ልገሳ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና ግንባታ፣ በሰላም ግንባታ እና ሌሎች ሥራዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ እየተሳተፉ ያሉ ወጣቶች ዕውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን በማበርከት ለተደራሽነት አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ሁሉ በመግባት አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነ ገልጸዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ትልቅ ስራ እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ከድር፤ የአቅመ ደካማ ዜጎችን ቤቶች መገንባት እና ማደስ ከፍተኛ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አብራርተዋል።

በዘንድሮ ክረምት የ3 ሺህ 420 ቤቶች ግንባታ እና የ2 ሺህ 200 ቤቶች እድሳት እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ እየተከናወነ በሚገኘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እስካሁን 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ወጣቶች ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገልጸው፤ በአጠቃላይ 10 ሚሊየን ያህል ወጣቶች ተሳትፎ ያደርጋሉ ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!