አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሉዓላዊነትና የእድገት ምልክት በመሆኑ መላው ኢትዮጵያውያን ያለልዩነት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጥሪ አቀረበ፡፡
ንቅናቄው ግድቡን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፥ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ የመጠቀም መብቷ ለድርድር እንደማይቀርብ በመግለጽ፤ የአባይ ወንዝን በፍትሃዊነት የመጠቀም ሉዓላዊ መብት እንዳላት አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
ኢትዮጵያ እንደ ህዳሴ ግድብ ባሉ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የምታከናውናቸው የኢነርጂ፣ የግብርና ማዘመንና የኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች ህጋዊ ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ እድገትና ቀጣናዊ መረጋጋት አስፈላጊ መሆናቸውን ነው ያስታወቀው፡፡
ግብጽ በዓባይ ውሃ ላይ በምታራምደው ጊዜው ያለፈበት፣ መሰረት የሌለውና ኢፍትሃዊ በሆነ ፍላጎት ምክንያት ኢትዮጵያ ከልማት ተከልክላ ልትቆይ አትችልም ሲል ፓርቲው በመግለጫው አስገንዝቧል፡፡
ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትከተለው አቋም ፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚደግፉ ዓለም አቀፍ ህጎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፥ ህዳሴ ግድብ የልዩነት ምንጭ ሳይሆን የተፋሰሱን ሀገራት ህዝቦች የሚያስተሳስር ነው ብሏል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከውስጣዊ የፖለቲካ ልዩነቶች የተሻገረ የልማት፣ የሉዓላዊነት እና የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ በመሆኑ ግድቡን መጠበቅ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ኃላፊነት መሆኑንም አስረድቷል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!