አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ140 ሚሊየን ብር በላይ ተገኝቷል፡፡
የክልሉ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ዳይሬክተር ሳሚ አብዱልዋሲ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ ከ160 ሺህ በላይ ጎብኚዎች ክልሉን ጎብኝተዋል፡፡
ከሌላው ጊዜ በተለየ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር መጨመሩን ገልጸው፤ የጁገል ግንብ፣ የማይዳሰሱ ባህላዊ ትውፊቶች፣ ባህላዊ ቅርሶችና ባህላዊ ቤቶች በሀገር ውስጥና በውጭ ቱሪስቶች ተጎብኝተዋል፡፡
በክልሉ መንግስትና በህብረተሰቡ ትብብር የተሠሩ የልማት ሥራዎች የክልሉን የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር አድርጓል ነው ያሉት።
የሸዋል ኢድ ፌስቲቫል በዩኔስኮ መመዝገቡ ጎብኚዎች እንዲመጡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉንም ገልፀዋል፡፡
ሐረር ከተማን የቱሪዝም መዳረሻነት ለማሳደግ እና ቱሪስቶችን ለመሳብ የሐረርን ባህልና ወግ ከማስተዋወቅ ባለፈ የጁገል ግንብ የዕድሳት ስራ መከናወኑን አስታወሰዋል።
በክልሉ በተሰሩ ስራዎች ከቱሪዝም ዘርፉ ከ140 ሚሊየን ብር በላይ መገኘቱንም አስረድተዋል፡፡
በየሻምበል ምህረት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!