አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ከከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመምከር ወደ አላስካ ግዛት አቅንተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች ዛሬ ምሽት ፊት ለፊት በመገናኘት እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
ከውይይቱ አስቀድሞ አላስካ የገቡት የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በሰጡት መግለጫ፤ ሀገራቸው አሜሪካ በቀላሉ የምትረዳውን ግልጽ የድርድር ሃሳብ ይዛ ትቀርባለች ብለዋል፡፡
የፕሬዚዳንት ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ሞስኮ በነበሩበት ወቅት ተስፋ ሰጭ ውይይት አድርገናል ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በሁለቱ ፕሬዚዳንቶች መካከል የሚደረገው ውይይት ሁሉንም ወገን አሸናፊ እንደሚያደርግ እምነታቸውን ገልጸዋል።
በዛሬ ምሽቱ የሁለቱ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች ውይይት የሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ዲፕሎማቶች ይገኛሉ መባሉን ሲኤንኤን እና አር ቲ ዘግበዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!