የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ450 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ ሆነዋል

By Abiy Getahun

August 15, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ክልል ሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳዮች ቢሮ በወጣቶች በተከናወነ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ450 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ ሆነዋል አለ።

በቢሮው የወጣቶች አደረጃጀት እና ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ ደመላሽ ያደቴ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶች ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ነው።

በክልሉ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ70 ሺህ በላይ ወጣቶችን ለማሳተፍ መታቀዱን ገልጸው፤ አረንጓዴ ዐሻራ፣ ሰላምና ጸጥታን ጨምሮ በ14 የስራ ዘርፎች ወጣቱን በማሳተፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል።

በዚህም እስካሁን 30 ሺህ የሚጠጉ ወጣቶች ተሳትፎ በማድረግ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት መስጠታቸውን ጠቅሰው፤ በአገልግሎቱ ከ450 ሺህ በላይ የሚሆኑ የማሕበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ሆነዋል ነው ያሉት።

በክልሉ እየተከናወነ የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ወጣቶች ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!