ፋና ስብስብ

የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታ በኦሮሞ ባህል እና እሴት መሰረት ሊከበር ይገባል – አባ ገዳ ጎበና ሆላ

By Abiy Getahun

August 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታ በኦሮሞ ባህልና እሴት መሰረት መካሄድ አለበት አሉ የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ።

አባ ገዳዎችና እና ሀደ ሲንቄዎች የጎቤና እና ሺኖዬ ጨዋታን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ÷ ጨዋታው ጥንታዊ የኦሮሞ ባህል እና እሴቶችን የተከተሉ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ጎቤ እና ሺኖዬን ከባህሉና ከገዳ እሴት ውጭ መጫወት የተከለከለ መሆኑን የገለጹት አባ ገዳ ጎበና ሆላ÷ ከባህላዊ እሴቱ ውጪ እንደ የገቢ ማስገኛ የሚጠቀሙበትና ባህሉን ለመበረዝ የሚጥሩ አካላትን አውግዘዋል፡፡

ጎቤ እና ሺኖዬ ወደ በጋው ብርሃን ሽግግር እና ለፀደይ ንጋት አቀባበል በክልሉ ሁሉም ቦታዎች በተለያዩ ቅርጾች የሚካሄድ ባህላዊ ጨዋታ እንደሆነም አንስተዋል።

ጨዋታውን ባለትዳር ያልሆኑ ከ12 እስከ 25 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ብቻ የሚሳተፉበት ሲሆን÷ ቄሮና ቀሬዎች በዘፈን፣ በመብላት እና በመጠጣት እንዲሁም ስጦታ እየተሰጣቸው የሚረከቡበት ነው።

ትዳር ያላቸው ሽማግሌዎች እና ጎልማሶች ደግሞ በየቤታቸው እየተቀበሏቸው ይመግቧቸዋል፤ ያጠጡዋቸው፤ ይባርኳቸዋልም።

በፀሐይ ጉሉማ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!