ስፓርት

በፖላንድ ሲለሲያ ዳይመንድ ሊግ የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ አሸነፈች

By Mikias Ayele

August 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) በፖላንድ ሲለሲያ ዳይመንድ ሊግ የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ አምስተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዘገብ አሸንፋለች።

አትሌቷ ተቃናቃኟን ኬኒያዊቷ ቢያትሪስ ቼቤት በፍጹም የበላይነት በመቅድም ነው በቀዳሚነት ውድድሩን ያጠናቀቀችው።

ጉዳፍ ውድድሩን በሶስት ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ከ62 ማይኮሮ ሴኮንድ በመግባት ያጠናቀቀች ሲሆን ያስመዘገበችው ሰዓት በርቀቱ 5ኛው የዳይመንድ ሊግ ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝገቧል፡፡