አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሎጂስቲክስ ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን።
ባለሥልጣኑ በሎጂስቲክስ ዘርፍ የሚስተዋለውን የሰለጠነ እና ብቁ የሰው ሃይል እጥረት ለመፍታት በትብብር እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ 100 ወጣት ሴቶችን በሎጂስቲክስ ዘርፍ ማሰማራት የሚያስችል ሥልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
ተማሪዎቹ በሞጆ ደረቅ ወደብ በመገኘት ከውጭ የሚገቡ እቃዎች በወደቡ በምን መልኩ እንደሚስተናገዱ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በባለሥልጣኑ የሞጆ አረንጓዴ ሎጂስቲክስ ማዕከል ግንባታ ሥራ አስኪያጅ ደሳለኝ ጌታሁን (ኢ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ወደቡ ከውጪ ከሚገባው እቃ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነውን እያስተናገደ ነው፡፡
ኢትዮጵያን በሎጂስቲክስ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ዘመኑን የዋጀ የሰው ኃይል ማፍራት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
ተማሪዎች በትምህርት ያገኙትን እውቀት በተግባር መመልከታቸው ለቀጣይ ሥራቸው ሥኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣኑ የሎጅስቲክስ አገልግሎቶችን የተሳለጡና እውቀት መር የሚያደርግ ስትራቴጂ በመተግበር ላይ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡
በሎጂስትክስ ዘርፉ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት መደረጉን የገለጹት ደግሞ በደረቅ ወደቡ የአካባቢ እና የማህበረሰብ ጥበቃ አማካሪ አቶ ብርሃን ኪዳን ናቸው፡፡
ወጣት ሴቶችን በሎጂስቲክስ ዘርፍ ለማሰማራት የተጀመረው ሥልጠና በዘርፉ ያለውን ክፍተት መሙላት እንደሚያስችልም ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!