የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በተሻለ ትጋትና ቁርጠኝነት መስራት ይገባል – አቶ አደም ፋራህ

By Melaku Gedif

August 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ሁሉም አመራርና አባላት በተሻለ ትጋት ሊሰሩ ይገባል አሉ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፍ የትጋት እና የስኬት ዓመት ነበር።

መላው የፓርቲ አመራርና አባላት በተባበረ ክንድ ተናበው መትጋት በመቻላቸው በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት።

በ2017 ዓ.ም በተሰሩ ሥራዎች 3 ዋና ዋና ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቁመው÷ እነዚህም የውስጠ ፓርቲ ጥንካሬ መጎልበት፣ የስትራቴጂያዊ ትብብርና አጋርነት መረጋገጥ እንዲሁም የሀገርና የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻል ናቸው ብለዋል፡፡

ህዝብ በልማት ተጠቃሚ እንዲሆን የተሰሩ ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩና በሰላምና መረጋጋት ረገድ የተሰሩ ሥራዎችም በሀገር ደረጃ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን እንዳስቻሉ መናገራቸውን ፓርቲው ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

2018 በጀት ዓመት ልዩ ዓመት መሆኑን የጠቀሱት አቶ አደም ፥ ሁሉም አመራርና አባላት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከባለፈው በጀት ዓመት በተሻለ ትጋትና ቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!