አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የደመወዝ ማሻሻያው የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ለማቃለል አይነተኛ ሚና ይኖረዋል አለ፡፡
የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ እንዳሉት፤ መንግስት የኑሮ ውድነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞችን የኢኮኖሚ ሁኔታ በማጤን የሠጠው ምላሽ ይደነቃል።
መንግስት ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ በቋሚ ገቢ ለሚተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች አንፃራዊ እፎይታ ይሰጣል፡፡
ማሻሻያው በአነስተኛ ደመወዝ እየሰሩ ያሉ ተቀጣሪዎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡
መንግስት ደመወዝ ከማሻሻል ባለፈ የመንግስት ሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል 6 ሺህ ብር እንዲሆን መወሰኑ ለዘመናት በሰራተኛው እና በኮንፌዴሬሽኑ ሲጠየቅ የነበረ ጥያቄ ፍሬያማ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
የደመወዝ ማሻሻያው ለታለመለት ዓላማ መዋል እንዲችል በየደረጃው የንግድ ስርዓቱ ላይ ጠንካራ ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
መንግስት የሠራተኞችን ደመወዝ በማሻሻል ያሳየውን ቁርጠኝነት የግል ድርጅቶችም ሊከተሉት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በጭማሪው የተካተተውን ዝቅተኛ የመንግስት ሰራተኛ የደመወዝ ወለል እንደ ተሞክሮ በመውሰድ በጅምር ላይ ያለውን የሠራተኛ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የመወሰን ስራ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲደረግ ፕሬዚዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል።
በሞሊቶ ኤሊያስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!