ዓለምአቀፋዊ ዜና

የትራምፕና ዘለንስኪ ውይይት በነጩ ቤተ መንግስት…

By Melaku Gedif

August 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በኋይት ሃውስ በድጋሚ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ፣ ሊኖሩ ስለሚችሉ የሰላም ጥረቶች፣ በአሜሪካ ድጋፍና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዚህ ወቅት ÷በጦርነቱ የሰዎችን ሞት ለማስቀረት የተኩስ አቁም ሃሳብን እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለአንድ ወገን ብቻ ስልታዊ ጥቅም በማይሆን መልኩ መደረግ እንዳለበት ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

“እኛ ሰላም ለማምጣት እየሰራን ነው” ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ÷ ለአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም ሳይሆን ሰፊና ዘላቂ የሰላም ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚገባ አስረድተዋል።

ቮሎድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው÷ ዩክሬን ጦርነቱን ለማቆም “ዲፕሎማሲያዊ መንገድ” ለመፈለግ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!