አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) በወቅታዊ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ ለፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የሚሰጠው ስልጠና ጀምሯል።
ስልጠናው “ወደ ተምሳሌት ሀገር: በተሻገረ ህልም፣ በላቀ ትጋት፣ አስተማማኝ ነገን መስራት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ መካሄድ የጀመረው።
ስልጠናው እስካሁን በተመዘገቡ የልማት እና መልካም አስተዳደር ሥራ አፈፃፀም፤ በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑን የፌዴራል ተቋማት የፓርቲ አደረጃጀቶች አስተባባሪዎች ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በወቅታዊ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው የፌዴራል ተቋማት አመራሮች ስልጠና ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት እንደሚሰጥ ብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!