አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተወዳጁ እና በጉጉት የሚጠበቀው የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የድምፃውያን ውድድር በነገው ዕለትም ቀጥሎ ይካሄዳል።
ወደ ፍጻሜው የቀረበው የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በየሳምንቱ አስደናቂም፤ አሳዛኝም ነገሮች እየታዩበት 11ኛ ሳምንት ላይ ደርሷል።
የነገ ተፋላሚዎች ማዕረግ ሃይሉ፣ ኤፍሬም ጌታቸው፣ ጴጥሮስ ማስረሻ፣ እየሩሳሌም አሰፋ፣ እዮቤል ፀጋዬ እና ናሆም ነጋሽ ሲሆኑ፤ ተወዳዳሪዎች ከሌላው ጊዜ በተለየ በጋራ የሚወዳደሩበት ዙር በጉጉት ይጠበቃል።
በነገው ዕለት በሚደረገው ውድድር እንደተለመደው አንድ እንግዳ በክብር ዳኛነት ይገኛል።
የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በሚያደርገው በፋና ላምሮት ውድድር በየሳምንቱ በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ አንድ ተሰናባች ይኖራል።
በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ይዞ የፍፃሜ ውድድሩን የሚያካሂደው ፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀለት ሲሆን፤ የዋናጫ እና የአዲስ ሙዚቃ ሽልማትንም ያበረክታል።
ይህን ደማቅ ውድድር በቀጥታ ስርጭት ልክ 6:00 ላይ በፋና ቴሌቪዥን፣ በፋና+ እና በሁሉም የፋና ዲጂታል አማራጮች ይከታተሉ።
በለምለም ዮሐንስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!