አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮሪደር ልማት ሥራ የአረንጓዴ ልማትን መሰረት በማድረግ እየተከናወነ ነው አለ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴዔታ የትምጌታ አስራት እንዳሉት ÷ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ዘላቂ የሀገር ግንባታ ሥራን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው፡፡
መርሐ ግብሩ መሰረተ ልማትን ከአረንጓዴ ልማት ጋር በማስተሳሰር የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም በሚያስችል መልኩ እየተተገበረ ነው ብለዋል፡፡
ዘላቂ የመሰረተ ልማት ግንባታ በኮሪደር ልማት ሥራው እየተከወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው ÷ ኢትዮጵያ እየሰራች ያለው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ የነገን ትውልድ ታሳቢ እንዳደረገም አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ አያሌው (ኢ/ር) በበኩላቸው ÷ የኮንስትራከሽን ዘርፉ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡
የግንባታ ዘርፉ ማካተት የሚገባቸውን መስፈርቶች እንዲያሟላ ትኩረት መደረጉን ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡
የኮሪደር ልማቱ የኮንስትራክሽን ዘርፉ የአረንጓዴ ልማትን ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ማስቻሉንም ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!