ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ የሩበን ዲያዝን ኮንትራት አራዘመ

By Melaku Gedif

August 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹን ሩበን ዲያዝ ኮንትራት ለተጨማሪ ዓመታት ማራዘሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ሩበን ዲያዝ በአዲሱ ኮንትራት መሰረት በማንቼስተር ሲቲ እስከ ፈረንጆቹ 2029 ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡

የ28 ዓመቱ ተጫዋች ማንቼስተር ሲቲን ከተቀላቀለ ወዲህ የአውሮፓ ሻምፒየንስ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡

ፖርቹጋላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ሩበን ዲያዝ በፈረንጆቹ 2020 ከቤኔፊካ ማንቼስተር ሲቲን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

ዲያዝ ኮንትራቱን ካራዘመ በኋላ ደስተኛ መሆኑን በመግለጽ ለማንቼስተር ሲቲ እና ለክለቡ ደጋፊዎች ክብር እንዳለው ተናግሯል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!