አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ2026 የዓለም ዋንጫ ዕጣ ድልድል በፈረንጆቹ ታህሳስ 5 ቀን 2025 በዋሽንግተን ዲሲ ይከናወናል አሉ።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ሲያስታውቁ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋቲኖ እና የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ተገኝተዋል።
የዕጣ ድልድሉ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኬኔዲ ማዕከል እንደሚደረግ ማስታወቃቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ጣምራ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን የ48 ሀገራት የእግርኳስ ብሔራዊ ቡድኖች በመድረኩ ይሳተፋሉ፡፡
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!