አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቀሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ሯች ባያክ እንዳሉት ÷ በክልሉ በግብርና፣ ማእድን፣ ኢንዱስትሪና ሌሎች ዘርፎች ለዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር ትኩረት ተደርጓል፡፡
በበጀት ዓመቱ በክልሉ ለሥራ እድል ፈጠራ ያሉ ምቹ የተፈጥሮ ጸጋዎችን በመጠቀም ለ24 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር በትብብር ይሰራል ብለዋል፡፡
እቅዱን ለማሳካትም ከባለፈው የተገኙት መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋትና ውስንነቶች በማረም በቅንጅት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የሚፈጠሩት የሥራ እድሎች ክህሎትን መሰረት ያደረጉ መሆናቸውንም ነው ኃላፊው ያስረዱት፡፡
በተለይም እንደ ሀገር የተጀመረውን የኮደርስ ስልጠና እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ለዘርፉ ስኬታማነትና ለክህሎት ግንባታ ሥራ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!