አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከደብረ ማርቆስ – ባሕርዳር በሚወስደው መንገድ የሚገኘው የጌደብ ወንዝ ድልድይ በነገው ዕለት ለተሽከርካሪ ክፍት ይደረጋል አለ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፡፡
አስተዳደሩ ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው ÷ በጎርፍ ጉዳት ደርሶበት የነበረውን የጌደብ ወንዝ ድልድይ በተገጣጣሚ ብረት የመገንባቱ ሥራ ተጠናቅቋል፡፡
ድልድዩ ነገ ነሐሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ለተሽከርካሪ ክፍት እንደሚደረግም አመልክቷል፡፡
የጌደብ ወንዝ ድልድይ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት ጮቄ ተራራ ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በደረሰበት ጉዳት ከደብረ ማርቆስ – ባሕርዳር የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ድልድዩ በጎርፍ ምክንያት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ግንባታው እስኪጠናቀቅ በትዕግስት ሲጠባበቁ ለቆዩ መንገደኞችና አሽከርካሪዎች ምስጋና ቀርቧል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!