ስፓርት

አርሰናል ኤዜን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ

By Yonas Getnet

August 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል እንግሊዛዊውን የአጥቂ አማካይ ኤቤሬቺ ኤዜ ከክሪስታል ፓላስ ማዘዋወሩን ይፋ አድርጓል።

መድፈኞቹ የ27 ዓመቱን ተጫዋች በ67 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ነው የግላቸው ያደረጉት፡፡

ተጫዋቹን ለማስፈረም ጫፍ ደርሰው የነበሩት ቶተንሃም ሆትስፐሮች በመጨረሻ ሰዓታት በከተማ ተቀናቃኛቸው አርሰናል ዝውውሩን መነጠቃቸው ይታወቃል።

ኤዜ ለአራት ዓመታት በኢምሬትስ የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲሆን፥ አርሰናል የተጫዋቹን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት የማራዘም አማራጭ እንዳለው ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!