የሀገር ውስጥ ዜና

በአሕፈሮም ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Yonas Getnet

August 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የመኪና አደጋው የደረሰው ዛሬ ንጋት 11፡00 ላይ ሴሮ ቀበሌ ልዩ ስሙ መቐልሕ በሚባል አካባቢ እንደሆነ የወረዳው የጸጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ሻምበል ገ/ትንሳዔ ገ/ገርግስ ለፋና ዲጅታል እንዳሉት፤ አደጋው የደረሰው ከእገላ ወረዳ ወደ እንትጮ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ነው።

አውቶቡሱ ከዋናው መንገድ በመውጣት 80 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል ውስጥ በመግባቱ በደረሰ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉንም ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ነው ያሉት።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን ገልጸው፤ የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ ነው ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!