የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ውስጣዊ አንድነትና ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጠናከር ይገባል

By Abiy Getahun

August 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ውስጣዊ አንድነትንና ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጠናከር ይገባል አሉ።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት አስመልክቶ “መገናኛ ብዙሃን ለብሔራዊ ጥቅምና ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ አውደ ጥናት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ‘ሚዲያ ለብሔራዊ ጥቅም’ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ሁሉም ዜጋ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሁለንተናዊ መንገድ ለማስከበር በአንድነት መረባረብ አለበት።

የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በሀሳብ የበላይነት መሞገትና ማክሸፍም እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለዚህም ውስጣዊ አንድነትና ሰላምን በማስጠበቅ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጠናከርና የዴሞክራሲ አቅም በመገንባት መረባረብ እንደሚገባ ማብራራታቸውውን ኢዜአ ዘግቧል።

መንግስት የኢትዮጵያን ብልፅግና በሁለንተናዊ መንገድ ለማረጋገጥ በሁሉም መስክ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው፤ መገናኛ ብዙሀን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር ላይ አጀንዳ ፈጥረው መስራት አለባቸው ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!