default

ቢዝነስ

በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን ያጠናክራሉ

By Abiy Getahun

August 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ዓለም አቀፍ መድረኮች የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን ለማጠናከር በር ከፋች ናቸው አሉ የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን፡፡

በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እና ተመራማሪ ሙሉጌታ ደበበ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ላይ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች የመገኘት ዕድላቸው ሰፊ ነው።

ይህም ከጉባኤዎች ጎን ለጎን ሀገራት ዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናሩ ያግዛል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የሚካሄዱ አህጉር እና ዓለም አቀፍ መድረኮች የሀገራት ትስስርን እና የዲፕሎማሲውን መስክ ለማጠናከር ትልቅ ዕድል ይፈጥራሉ ያሉት ደግሞ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር ጥላሁን ሊበን ናቸው።

በኢትዮጵያ የሚካሄዱ መድረኮች የዲፕሎማሲ ግንኙነት በማስፋት ሀገራት ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ አንስተዋል።

ጉባኤዎቹ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ እና የሀገርን ገጽታ የሚገነቡ በመሆናቸው ዲፕሎማቶችም ሆኑ ሌሎች አካላት ለዘርፉ ስኬት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ምሁራኑ አስገንዝበዋል፡፡

ጉባኤዎቹ በኢትዮጵያ መካሄዳቸው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአህጉሪቱም ኩራት እንደሆነ ተናግረዋል።

በስንታየሁ አበበ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!