አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን በገንዘብ መርዳት የሚያስችሉ መንገዶችን ለመዝጋት ጠንካራ እና ቁርጠኛ በሆነ መንገድ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች አለ።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ ለፋና ሚድያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ ተቋሙ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አጠራጣሪ ግብይቶችን በመከላከል ሽብርተኝነትን ለመቆጣጠር ፋይናንስ እና ፋይናንስ ነክ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ይሰራል።
ከአጠራጣሪ ግብይቶች በመነሳት ትንታኔ ተሰርቶ፣ ወደ ሀገር የሚገባ እና ከሀገር የሚወጣ ገንዘብን ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።
ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር ተጨማሪ ምርመራ በማድረግ ሀብት እስከማስመለስ የሚደርስ ተግባር መከናወኑንም ጠቁመዋል።
ሙስና ፣ ታክስ መሰወር፣ በህገ ወጥ ሃዋላ የተገኘ ገንዘብ እና ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል የህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀሎች ምንጭ መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ እነዚህን ወንጀሎች ለመከላከል ጥናት በማድረግ የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት የተቋማት አደረጃጀት እና ግንባታ አከናውናለች ነው ያሉት።
ተቋማት አጠራጣሪ ግብይቶችን ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የመላክ ግዴታቸው እንዲወጡ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸው፤ ተቋማቱ መረጃ የሚልኩበት የበይነ መረብ ስርዓት መኖሩን አመልክተዋል።
ተቋማት በሚልኳቸው አጠራጣሪ የገንዘብ ዝውውር መረጃዎች መሰረት ውሳኔዎች እየተሰጡ እና ተጠርጣሪዎች እየተያዙ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከ17 ሀገራት ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ገልጸው፤ ግብይቶች፣ የገንዘብ ዝውውሮችና የሸሹ ሀብቶች ላይ በቅንጅት የምርመራ እና የመረጃ ልውውጥ የሚደረግበት አሰራር መኖሩን ተናግረዋል።
በዚህም ትልቅ ውጤት መገኘቱን አንስተው፤ ሽብርተኞችን በገንዘብ መርዳት የሚያስችሉ መንገዶችን ለመዝጋት ኢትዮጵያ ጠንካራ እና ቁርጠኛ በሆነ መንገድ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች ነው ያሉት።
በሽብርተኝነት የተፈረጁ አካላት ከፋይናንስ ተቋማቶቻችን ጋር በመቀናጀት ግብይት እንዳይፈጠር እና የገንዘብ ማዘዋወሪያ መንገድ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ የሚደረግበት የተጠናከረ ስርዓት እንዳለ ጠቁመዋል።
ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ የሽብርተኞች መንገድ እንዳትሆን አድርገናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በአልማዝ መኮንን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!