አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የምረቃ ዋዜማ ላይ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በራስ አቅም ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ እንደሚቻል ያስተማረ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው አሉ።
አምባሳደር ሱሌይማን ከዩኒቨርሳል ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ የህዳሴ ግድቡ የቀጣናውን ህዝቦችን በማስተሳሰር የቀጣናውን አንድነት ያጠናክራል።
ግድቡ ኢትዮጵያውያን ድህነትን በመዋጋት የተሻለ ኑሮ ለመኖር የሚያደርጉትን ትግል የሚያግዝ መሆኑን ገልጸው፤ የቀጣናውን ራዕይ እውን ለማድረግ መሰል ፕሮጀክቶችን ለመገንባት መንገድ የከፈተ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ህዳሴ ግድቡ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ ከባድ ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ግን በተባበረ ክንድ አሳክተውታል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የሚያስችል ድጋፍ ለማግኘት ያደረገችው ሙከራ በውጭ ኃይሎች ያልተገባ ጫና እና ዘመቻ ሳይሳካ መቅረቱን አስታውሰው፤ ኢትዮጵያ ግድቡን በራሷ አቅም ለመገንባት የደረሰችበት ውሳኔ ፍሬ አፍርቷል ነው ያሉት።
የአንድነት ምልክት የሆነው የህዳሴ ግድብ የናይል ተፋሰስ ሀገራትን አንድ እንደሚያደርግ ገልጸው፤ በተለይም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስገንዝበዋል።
ግድቡ ተጠናቆ የምረቃ ዋዜማ ላይ መገኘቱ ለአፍሪካ ትልቅ ድል ነው ያሉት አምባሳደር ሱሌይማን፤ በራስ አቅም ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ እንደሚቻል ያስተማረ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!