ቴክ

በኔቫዳ በደረሰ የሳይበር ጥቃት የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አቋረጡ

By abel neway

August 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ኔቫዳ ግዛት በደረሰ የሳይበር ጥቃት የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ድረገጾች አገልግሎት ማቋረጣቸው ተሰማ፡፡

የኔቫዳ ግዛት ገዢ ጆ ሎምቦርዶ የሳይበር ጥቃቱ የደረሰው ባለፈው እሁድ ማለዳ ሲሆን ቢሮዎች እና ድረገጾች ሰኞ እና ማክሰኞ ተዘግተዋል ብለዋል፡፡

በጥቃቱ የመንግስት ቢሮዎች ኢላማ መደረጋቸውን ገልጸው፤ ጥቃቱ ስለፈጸመው አካል ምንም አይነት ተጨባጭ መረጃ አለመገኘቱን ጠቅሰዋል።

የችግሩን ምንጭ ለማወቅ በመንግስት በኩል ምርመራ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የግዛቱ መንግስት ድረ ገጽ እንዲሁም የስልክ መስመር አገልግሎት እየሰጠ አይደለም ያሉት ጆ ሎምቦርዶ፤ የአስተዳደር ቢሮው የአደጋ ጊዜ የስልክ መስመር እና ሌሎች ወሳኝ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል።

የተቋረጡ አገልግሎቶች ሲጀመሩ የሚገለጽ መሆኑን ያመለከተው የዋሽንግተን ታይምስ ዘገባ፤ ቢሮዎች በኦንላይን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እያደረጉ ነው ብሏል።