የሀገር ውስጥ ዜና

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች…

By Melaku Gedif

August 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በመጪው መስከረም ወር የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በተለያዩ ከተሞች ይጀመራል።

የኦሮሚያ ክልል የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ዳምጠው ገመቹ እንዳሉት ÷ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በክልሉ 4 ከተሞች ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቅቋል፡፡

አገልግሎቱ የሚጀመርባቸው ከተሞች አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሸገር እና ሻሸመኔ መሆናቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

በቀጣይ በሁለተኛ ዙር በ19 ከተሞች አገልግሎቱን የማስፋት ሒደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ዳምጠው አረጋግጠዋል፡፡

የአማራ ክልል የሰው ሃብትና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ ባንቺአምላክ ገ/ማሪያም በበኩላቸው ÷ ከመስከረም ወር ጀምሮ በባሕርዳር፣ ደሴና ጎንደር ከተሞች የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ወደ ሥራ ይገባል ብለዋል።

ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ኮምቦልቻ እና ደብረ ታቦር ከተሞች ደግሞ በሁለተኛ ዙር አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመሩ አመልክተዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!