የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን የአየር ኃይል ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

By Abiy Getahun

August 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በሁለቱ ሀገራት አየር ኃይሎች መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ከፓኪስታን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ኤር ቺፍ ማርሻል ዛሂር አህመድ ባበር ሲዱ ጋር በኢስላም አባድ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የመከላከያ ሠራዊትን በዘመናዊ መልክ ለማዋቀር ስልታዊ ትኩረትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል።

የፓኪስታን አየር ኃይል ያለውን ጠንካራ የተግባር ዝግጁነት፣ እያደገ የመጣውን ሁለገብ ዘርፍ ችሎታዎች እና አስተማማኝ የመከላከል አቋም አድንቀዋል።

ኤር ቺፍ ማርሻል ዛሂር አህመድ ባበር ሲዱ በበኩላቸው፤ ጉብኝቱ በሀገራቱ መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት እንደሚያሳይ ገልጸዋል።

ፓኪስታን ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ከፍተኛ ዋጋ እንደምትሰጥ ገልጸው፤ የሀገራቸው አየር ኃይል በአቅም ግንባታ፣ በላቀ ስልጠና እና በክንውን ዘርፎች ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ድጋፍ ለማድረግ ጽኑ አቋም እንዳለው አረጋግጠዋል።

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)፤ ጉብኝቱ በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት አየር ኃይሎች መካከል ለአዲስ ስልታዊ የትብብር ምዕራፍ ጠንካራ መሰረት መጣሉን ገልፀዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!