ቢዝነስ

አየር መንገዱ ወደ ያቤሎ በረራ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቀቀ

By Yonas Getnet

August 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ ሶስት ሳምንታዊ በረራዎችን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቅቋል።

አየር መንገዱ ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ስራ ወደሚጀምረው የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ በረራ ለመጀመር መዘጋጀቱን ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አስታውቋል።

ያቤሎ እና አካባቢው ከፍተኛ የቀንድ ከብት እርባታ የሚካሄድበትና ለእርሻ የሚውል ሰፊ መሬት ያለበት ስፍራ በመሆኑ አውሮፕላን ማረፊያው ለአካባቢው ማህበረሰብ ኢኮኖሚያው እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል።

ከዚህም ባለፈ በአካባቢው ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክር ነው።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!