አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ሁለት ወራት በብርቱ ፉክክር እየተካሄደ አምስት ተወዳዳሪዎች ብቻ የቀሩት የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በነገው ዕለት ይካሄዳል።
ተወዳዳሪዎቹ ወደ ፍጻሜው ለማለፍ ብርቱ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።
ለፍፃሜ የሚቀርቡት አራት ተወዳዳሪዎች ሲሆኑ የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በማድረግ በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ አንድ ተሰናባች ይኖራል።
በውድድሩ አንድ እንግዳ በክብር ዳኛነት ይገኛል።
በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ይዞ የፍፃሜ ውድድሩን የሚያካሂደው ፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀለት ሲሆን፤ የዋናጫ እና የአዲስ ሙዚቃ ሽልማት ያበረክታል።
ይህን ደማቅ ውድድር በቀጥታ ስርጭት ነገ ቅዳሜ ከ6:00 ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን፣ በፋና+ እና በሁሉም የፋና ዲጂታል አማራጮች ይከታተሉ።
በለምለም ዮሐንስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!