የሀገር ውስጥ ዜና

በአርሲ ዞን በአነስተኛ አውሮፕላን የታገዘ የጸረ አረም ኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው

By Yonas Getnet

August 29, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርሲ ዞን በአነስተኛ አውሮፕላን የታገዘ የጸረ አረም ኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው አለ የናሽናል ኤር ዌይስ።

የናሽናል ኤር ዌይስ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዘኸኝ ብሩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ ወደ ሀገር ውስጥ በገቡ የኬሚካል መርጫ አውሮፕላኖች በመታገዝ እየተከናወነ ያለዉ የኬሚካል ርጭት ምርታማነትን ያሳድጋል።

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደጀኔ ሂርፖ በበኩላቸው፤ በሰብል እንክብካቤ የመጨረሻዉን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራን ነው ብለዋል።

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የጸረ አረም እና የጸረ ተባይ ኬሚካል ርጭት የዚህ ማሳያ መሆኑን በአብነት አንስተው፤ እንዲህ አይነት ቴክኖሎጂ መጠቀም ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ዘመናዊ ግብአቶችን በመጠቀም ዘርፉን በማዘመን የምርት ጥራትና ብዛትን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአርሲ ዞን አስተዳዳሪ ኢብራሂም ከድር ዞኑ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ቀዳሚ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም የአካባቢውን አምራችነት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

ኤር ትራክትር 02 እና ድሮንን በመጠቀም ከ1 ሺህ 200 ሄክታር በላይ የአንድ ጊዜ ርጭት ማከናወን እንደተቻለም አመልክተዋል።

በኦሊያድ በዳኔ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!