አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር 30 ተቋማትን በማስተሳሰር የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀላጥፍ ”ቼቼ” የተሰኘ መተግበሪያ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
የአስተዳደሩ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ ኃላፊ አብዱላዚዝ ሻፊ እንዳሉት÷ ወጣቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ከማብቃት ባለፈ የሥራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና 7 ሺህ 832 ወጣቶችን ለማሰልጠን ታቅዶ ከ14 ሺህ በላይ ወጣቶች ሥልጠናውን እንደወሰዱ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን የወሰዱ ከ11 ሺህ በላይ ወጣቶች ከኢንዱስትሪና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር የሥራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡
በአስተዳደሩ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች በተለይም በመንግስት ተቋማት የሚሰጥ አገልግሎት እንዲሻሻል እያገዙ ነው ብለዋል፡፡
ዜጎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ”ቼቼ” የተሰኘ መተግበሪያ በልጽጎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም አመልክተዋል፡፡
መተግበሪያው 30 ተቋማትን በማስተሳሰር 500 የሚጠጉ አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡
በተስፋዬ ሃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!