ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና እና ህንድ ከተፎካካሪነት ወደ አጋርነት

By Abiy Getahun

August 31, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የረጅም ጊዜ የድንበር ውዝግብን ጨምሮ ከዓመታት ውጥረት በኋላ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

ከሰባት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በተሳተፉበት የሻንጋይ የትብብር ድርጅት (SCO) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በቻይና የወደብ ከተማዋ ቲያንጂን ተገናኝተዋል።

መሪዎቹ ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እንዳሉት፤ ሁለቱ ሀገራት ተፎካካሪዎች ሳይሆን አጋሮች መሆን አለባቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በበኩላቸው፤ በሀገራቱ መካከል የሰላምና መረጋጋት ድባብ ተፈጥሯል ብለዋል።

በፈረንጆቹ 2020 በመካከላቸው ተፈጥሮ በነበረው የድንበር ግጭት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የአውሮፕላን በረራ በቅርቡ እንደሚጀምር ማመልከታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጨምሮ ከ20 በላይ የሀገራት መሪዎች፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎች ይገኛሉ።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!