ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ በብራይተን ተሸነፈ

By Mikias Ayele

August 31, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በብራይተን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ጀምስ ሚልነር በፍፁም ቅጣት ምት እና ግሩዳ ሲያስቆጥሩ የማንቼስተር ሲቲን ብቸኛ ግብ ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ በሊጉ ተከታታይ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡

በሌላ ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የ3ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት 30 ላይ በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ሊቨርፑልን ከአርሰናል ያገናኛል፡፡