ስፓርት

በሜክስኮ ማራቶን አትሌት ታዱ አባተ አሸነፈ

By Mikias Ayele

August 31, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሜክሲኮ የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ታዱ አባተ አሸንፏል፡፡

አትሌቱ  ርቀቱን  2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመጨረስ ነው ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው፡፡

በርቀቱ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አዳነ ከበደ 2 ሰዓት ከ13 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት አራተኛ ደረጃን ይዟል፡፡