የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቁ

By Melaku Gedif

September 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በሲዳማ ክልል የተገነቡ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን መርቀው ከፍተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም አቶ አደም በሀዋሳ ከተማ ዳካ ክ/ከተማ የሚገኘውን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ባለ 5 ወለል ሕንጻ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

አመራሮቹ በሀዋሳ ከተማ የተከናወነውን ኮሪደር እና ሌሎች የልማት ሥራዎችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በጥላሁን ይልማ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!