አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት 331 የወረዳ ፍርድ ቤቶች እና 25 ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችን በቴክኖሎጂ የማስተሳሰር ስርዓት ተፈጥሯል አለ።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ ዳኛ ፈዬራ ሀይሉ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ በክልሉ የሚገኙ ፍርድ ቤቶችን በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር በክልሉ በሁሉም አቅጣጫ በኢ-ፋይሊንግ አገልግሎት እየተሰጠ ነው።
የተለያዩ ጉዳይ ያላቸው ተገልጋዮች ሳይጉላሉ ባሉበት ሆነው በይግባኝ፣ በቪድዮ ኮንፍረንስ ክርክራቸውን በማድረግ የዳኝነት አገልግሎቱን እንዲያገኙ መደረጉንም አንስተዋል።
በክልሉ ቀደም ሲል አሮጌና ለዳኝነት አገልግሎት አስቸጋሪ የነበሩ የችሎት ማስቻያዎችን ለዳኝነት አገልግሎት ምቹ በማድረግ የማሻሻያና የማስፋፊያ ስራዎችን በተለያዩ ፍርድ ቤቶች እንዲሰራ ተደርጓል ብለዋል።
በተጨማሪም በአሁን ወቅት በክልሉ በአዲስ እንዲደራጁ ለተደረጉት የምስራቅ ባሌ ዞን እና የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ህንጻ ግንባታ ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።
በክልሉ ከመስከረም 22 ቀን ጀምሮ መደበኛ የፍርድ ቤት አገልግሎት እንደሚጀመር አንስተው፤ በአሁኑ ወቅት ዳኞች ውዝፍ መዝገቦችን በማጥራትና የዜጎችን መብት ለማስከበር በተረኛ ችሎት የተለያየ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም አመልክተዋል።
በታሪክ አዱኛ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!