የሀገር ውስጥ ዜና

የዜጎችን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው – አቶ ሙስጠፌ

By Melaku Gedif

September 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ የዜጎችን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በቶጎጫሌ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታን አስጀምረዋል።

አቶ ሙስጠፌ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የዜጎችን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ውጤት ተገኝቷል፡፡

የሆስፒታልና ት/ቤቱ ግንባታዎች ሲጠናቀቁ ለአካባቢው ማሕበረሰብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ሙሴ አሕመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ ሆስፒታሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የቀዶ ጥገና፣ የእናቶችና ሕጻናት ሕክምና እንዲሁም ለተኝቶና ለተመላላሽ ሕክምና አገልግሎት መስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡

መንግስት ለትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ያነሱት ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ መሃመድ ሼክ አደን ናቸው።

በተስፋዬ ሃይሉ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!