ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ ዶናሩማን አስፈረመ

By Abiy Getahun

September 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲ 30 ሚሊየን ዩሮ ወጪ በማድረግ ጣሊያናዊውን ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማን ከፒኤስጂ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ዶናሩማ በማንቼስተር ሲቲ ቤት እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ የሚያቆየውን ኮንትራት ተፈራርሟል፡፡

ግብ ጠባቂው በ2024/25 የውድድር ዓመት ፒኤስጂ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ሲያሳካ ትልቁን አስተዋፅኦ ማርከቱ አይዘነጋም፡፡

ማንቼስተር ሲቲ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂውን ኤደርሰን ሞራይስን ለቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ አሳልፎ መስጠቱን ተከትሎ ዶናሩማን የእሱ ተተኪ በማድረግ አስፈርሟል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!