ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ሺ ፍትሃዊ የዓለም አቀፍ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ሀገራት በጋራ እንዲሰሩ ጠየቁ

By Abiy Getahun

September 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ሀገራት የበለጠ ፍትሃዊ የሆነ የዓለም አቀፍ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት በሰሜን ቻይና በምትገኘው በቲያንጂን ከተማ በተካሄደው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ስብሰባ ላይ ነው፡፡

የዓለም አስተዳደር ኢኒሼቲቭ ሉዓላዊ እኩልነትን ማክበር፣ ዓለም አቀፍ የህግ የበላይነትን ማክበር፣ ባለብዙ ወገንተኝነትን መለማመድ፣ ህዝብን ያማከለ አካሄድን መደገፍ እና ተጨባጭ ርምጃዎችን በመወሰድ ላይ ያተኮረ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

አዳዲስ ስጋቶችና ፈተናዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውን ጠቅሰው፤ ዓለም አዲስ የእንቅስቃሴ እና የለውጥ ወቅት ውስጥ ገብታለች ነው ያሉት።

የተባበሩት መንግስታት በዓለም አቀፍ አስተዳደር ውስጥ የማይተካ ቁልፍ ሚናውን ማረጋገጥ እንዳለበትም አመላክተዋል።

ሁሉም ሀገራት በጥንካሬ እና ሃብት ሳይገደቡ እኩል ተሳታፊ፣ ውሳኔ ሰጪ እና በዓለም አቀፍ አስተዳደር ተጠቃሚ መሆን አለባቸው ብለዋል።

የሻንጋይ የትብብር ድርጅት የመሪነት ሚናውን በመጫወት እና የዓለም አስተዳደር ኢኒሼቲቭን በማስፈፀም ረገድ አርአያ ለመሆን እና በዚህ ተለዋዋጭ ዓለም የመረጋጋት ሃይል ሆኖ መቀጠል አለበት ነው ያሉት።

በዓለም አቀፍ የአስተዳደር ኢኒሼቲቭ ስብሰባ ላይ ከ20 በላይ ሀገራት መሪዎች እና የ10 ዓለም አቀፍ ድርጅት መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!