ቢዝነስ

የአዲስ አበባ ከተማ የገበያ ማዕከላት የንግድ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተከፈተ

By Abiy Getahun

September 03, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የገበያ ማዕከላት የንግድ ኤግዚቢሽን እና ባዛር በአራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎትና አፍሪካ ሕብረት በሚገኙት ማዕከላት በዛሬው ዕለት ተከፍቷል።

ኤግዚቢሽንና ባዛሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተከፍቷል።

የገበያ ማዕከላቱ ባዛር ለመጭው በዓል የሚሆኑ የተለያዩ ግብአቶች ቀርበውበታል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንዳሉት÷ በማዕከላቱ የተከፈተው የንግድ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ሸማቹን ከአምራቹ ጋር በቀጥታ በማገናኘት በበዓል ወቅት የሚያጋጥመውን ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ለመከላከል ያስችላል፡፡

በተጨማሪም የገበያ ማዕከላቱ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች የማህበረሰቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የሚሳዩ ናቸው ብለዋል፡፡

ለመጭው በዓል በማዕከላቱ ከተከፈቱ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች በተጨማሪ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚሸጡ ባዛሮች በሁሉም ክፍለ ከተሞች ይከፈታሉ ተብሏል፡፡

በቅድስት አባተ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!