ዓለምአቀፋዊ ዜና

ጆ ባይደን ከቆዳ ካንሰር ህመም ጋር በተያያዘ የቀዶ ህክምና አከናወኑ

By Mikias Ayele

September 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከቆዳ ካንሰር ህመማቸው ጋር በተያያዘ የቀዶ ህክምና አከናውነዋል።የ82 ዓመቱ አዛውንት ጆ ባይደን ቃል አቀባይ እንዳሉት÷ ባይደን ካጋጠማቸው የቆዳ ካንሰር ህመም ጋር በተገናኘ ያደረጉትን የቀዶ ህክምና በስኬት አጠናቀዋል፡፡

ህክምናው በካንስር የተጠቁ የቆዳ ክፍሎችን ማስወገድ መሆኑን የጠቀሱት ቃል አቀባይዋ÷ ባይደን ከህክምናው በኋላ ስላሉበት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ሲቢኤስ የዜና አውታርን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው÷ ጆ ባይደን ከሰሞኑ በቀኝ በኩል ባለው የጭንቅላታቸው ክፍል ላይ ቁስል ታይቷል፡፡

በተደጋጋሚ በካንሰር ህመም እየተጠቁ የሚገኙት ባይደን፤ ባላፈው ግንቦት ወርም ወደ አጥንታቸው እንደተሰራጨ በተገለፀው የፕሮስቴት ካንስር ተይዘውም ነበር፡፡

ጆ ባይደን በወቅቱ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ካንሰር ሁላችንንም ይነካል፤ እንደማንኛው የካንሰር ታማሚ እኔ እና ባለቤት ጂል በጥንካሬ እንቆማለን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው በፊት ተደጋጋሚ የቆዳ ካንስር ህክምና አድርገዋል።

በሚኪያስ አየለ